ዋና ከተማ

Article on other languages:

del.icio.us del.icio.us
Digg Digg
Furl Furl
Reddit Reddit
Rojo Rojo
Add to OnlyWire

ዋና ከተማ የአገር ወይም የክፍላገር መንግሥት የሚገኝበት ማእከላዊ ከተማ ነው። ባለ ሥልጣኖች ሹሞችና መሪዎች ይሠሩበታል።

ብዙ ጊዜ ዋና ከተማ የአገሩ ትልቁ ከተማ ይሆናል። ለምሳሌ ሞንቴቪዴዮኡሩጓይ ታላቁ ከተማ ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ ዋና ከተማው ነው። ቢሆንም ዋና ከተማ ሁልጊዜ ያገሩ አንደኛው ትልቅ ከተማ አይደለም። ለምሳሌ የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ሲሆን ከአንደኛው ትልቅ ከተማው ግን ከኒው ዮርክ ከተማ ያንሳል። እንዲሁም የሕንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊ ከታላቁ ከተማ ከሙምባይ በጣም ያንሳል።

አንዳንድ አገር ከ1 በላይ ዋና ከተማ አለው። ለምሳሌ ቦሊቪያ ሁለትና ደቡብ አፍሪካ ሦስት ዋና ከተሞች አሉት። ናውሩ ምንም ይፋዊ ዋና ከተማ የሌላት የሰላማዊ ውቅያኖስ ደሴት አገር ናት። አንዳንድ አገሮች ደግሞ የዋና ከተሞቻቸውን ሥፍራ በየጊዜው ያዛውራሉ።

This article is from Wikipedia. All text is available under the terms of the GNU Free Documentation License.


Giant Panda

Mercedes Car
James Bond Guide
This site monitored by SitePinger.net